“ጳጉሜን ለጤና”

Image

የውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ከጳጉሜን 1 እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ ባሉት አምስት ቀናት የመክፈል አቅም ለሌላቸው ሕሙማን ነፃ የሲቲ ስካን ምርመራ አገልግሎት እንደሚሰጥ ትናንት አስታወቀ፡፡

የማዕከሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ኃይሉ እንደገለጹት ማዕከሉ “ጳጉሜን ለጤና” በሚል መርህ ነፃ  አገልግሎቱን የሚሰጠው አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ አገሪቱ ከሚገኙ የመንግሥት ሆስፒታሎች ምርመራ እንዲያደርጉ ወረቀት ለተጻፈላቸው ሕሙማን ብቻ ነው፡፡

የሲቲ ስካን ምርመራ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ከመሆኑም አንፃር በርካታ ዜጎች አገልግሎቱን ማግኘት ለብዙዎች ከባድ ነው፡፡ በመሆኑም አቅም ለሌላቸውና በገንዘብ እጦት ምርመራውን ማድረግ ላልቻሉ ማዕከሉ የዚህ ዓይነቱን ነፃ አገልግሎት ሲሰጥ የአሁኑ ለአራተኛ ጊዜ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

“ጳጉሜን የተመረጠበትም ምክንያት፣ ጳጉሜን ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ያለች ብቸኛ ወር መሆኗ ለየት ስለሚያደርጋት፣  አሮጌውን ዓመት ትተን ወደ አዲሱ ዓመት የምንሸጋገርበት ወር ስለሆነና፣ ከአዲሱ ዓመት ጋር ጤናን፣ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ መቻቻልን፣ አብሮነትን ይዘን ስለምንሄድ፣ ለሙስሊሙም ሆነ ለክርስቲያን የአዲስ ዓመት በዓል ሁላችንንም አንድ የሚያደርገን ወር በመሆኗ ነው” ብለዋል፡፡

ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል 16 ስላይስ የሆነ አዲስ የሲቲ ስካን ማሽን ያስመጣ ሲሆን ኤምአርአይ የተባለውንም መሳሪያ ለማስመጣትና ሥራ ላይ ለማዋል የሚያስችል ዝግጅት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ዶ/ር ተስፋዬ ከበደ የውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ራዲዮሎጅስት “ሲቲ ስካን ማለት ሲተነተን ኮምፒተራይዝድ ቶሞግራፊ ማለት ሲሆን የሚሠራውም እንደማንኛውም የኤክስሬይ ማሽኖች ጨረርን በመጠቀም ነው፡፡ ከሌሎቹ ማሽኖች የሚለየው እያንዳንዱን የሰውነት ክፍል በመከፋፈል በሰውነት ውስጥ ያሉትን አካላት በሙሉ የሚያሳይ ዓለም ከደረሰበት ከፍተኛ የሕክምና ምርመራ ቴክኖሎጂዎች አንዱ የሆነ የምርመራ መሳሪያ መሆኑ ነው” ብለዋል፡፡

ምርመራው በሽታዎች ከመከሰታቸው በፊት ገና በእንጭጭነታቸው ዲቴክት ወይም ዲያግኖስ ለማድረግ ይረዳል፡፡ በሽታውም ከተዛመተ በኋላ በሽታው የሄደበትን ቦታዎችና ያለበትን ደረጃ በማሳወቅ ለሚቀጥለው ሕክምና መስመር ያበጃል፡፡ የሚሰጠው ጥቅም ከፍተኛ ቢሆንም እንደማንኛውም የጨረራ መሳሪያ የራሱ የሆኑ ጉዳቶች አሉት፡፡

ምርመራው ከሐኪም ትዕዛዝ ውጭ ሕሙማን ወይም ግለሰቦች መጥተው ይሄንን አካሌን በዚህ መሳሪያ መመርመር እፈልጋለሁ ብለው የሚመረመሩት ምርምራ ሳይሆን በሐኪም ትዕዛዝ ብቻ የሚሰጥ እንደሆነ ነው ራዲዮሎጅስቱ የተናገሩት፡፡

ኅብረተሰቡ አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ማዕከሉ ሲመጣ በተለይ ሕፃናትና በመውለድ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች በሐኪም የታዘዘ ወረቀት ይዘው መምጣት እንደሚገባቸው፣ እርግዝና አለን ብለው የሚጠረጥሩና ሴቶች ነገሩን ማረጋገጥ እንዳለባቸው፣ ምክንያቱም መሳሪያው በጨረር የሚከናወን እንደመሆኑ መጠን በውስጥ ሳይታወቅ በነበረ እርግዝና ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡

አቶ ስሩር ከድር የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጨረራ  አመንጪዎች ሥራ ላይ ሲውሉ በአግባቡ ደረጃቸውን ጠብቀው፣ አስፈላጊውን የቁጥጥር መስፈርት አሟልተውና በፍቃድ ሥርዓት ማለፍ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ “ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ሥራ ላይ እንዲውሉ ያስፈለገበትም ምክንያት በአጭርና በረጅም ጊዜ በጤና ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ በመሆናቸው ነው” ብለዋል፡፡

ኤክስሬይ በሚታዘዝበት ሰዓት በትክክለኛ  ባለሙያ መታዘዝ እንዳለበት፣ የሚታዘዘውም ጉዳቱና ጥቅሙ ተመዝኖ ሲሆን ከታዘዘም በኋላ በትክክለኛ ባለሙያ ኤክስሬይው መነሳት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ መሳሪያውም ጥራቱን የጠበቀና በአንድ እይታ ብቻ የኤክስሬው መረጃ የሚገኝበትን ሁኔታ መፍጠር እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s