ሁሉም የ10/90 ተመዝጋቢዎች በመጭው ዓመት የቤት ተጠቃሚ ይሆናሉ

Image

የ10/90 የቤት ተመዝጋቢዎች በ2006 ዓም ሙሉ በሙሉ የቤት ባለቤት እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝ የ10/90 የቤት ተመዝጋቢዎች ቁጥር 23 ሺህ 5መቶ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ አን በግንባታ ላይ ያሉት ቤቶች ቁጥር ደግሞ 24 ሺህ 5 መቶ ነው፡፡ ቀሪው 1ሺህ ቤት በቀጣይ በልማት ተነሽ ለሚሆኑ ከሚያስፈልገው የ6ሺህ ቤት ውስጥ እንደሚካተትም ተናግረዋል፡፡ ይህም የፍላጎትና የአቅርቦት አለመመጣጠንን ያስከተለ በመሆኑ ከቀጣይ አመት ጀምሮ የ10/90 የቤት መርሃ ግብሩ እንደማይኖር ገልጸዋል፡፡

ዋና ስራ አስኪያጁ እንደሚሉት የ20/80 መርሀ ግብር  ለነባር ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ ይሰጣል ብለዋል፡፡  ቀሪ ነባር ተመዝጋቢዎች በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታትና አዲስ የ20/80 ተመዝጋቢዎች ደግሞ በቀጣይነት የቤት ባለቤት እንደሚሆኑ ጠቁመዋል፡፡

አሁን እየተገነቡ ካሉት የ10/90 ቤቶች ግንባታ 40 በመቶ ሥራቸው እንደተጠናቀቀ የገለጹት አቶ ይድነቃቸው ፣ሌሎቹ ለቀጣዩ አመት የሚተላለፉ የኮንዶሚኒየም ግንባታዎች ደግሞ 70 በመቶ እንደተጠናቀቁ ተነግረዋል፡፡

በ2006 ዓ.ም የሚተላላፉት ቤቶች የመሰረተ ልማት በተለይም የውሃና መብራት ችግር እንዳያጋጥም በ9መቶ ሚሊዮን ብር አስፈላጊ መሰረተ ልማት የማሟላት ተግባራት በሂደት ላይ እንደሆኑም ስራ አስኪያጁ አስረድተዋል፡፡

በዚህ ዓመት አና ከባለፉት አመታት የተዛወሩና አዲስ የተጀመሩትን ጨምሮ 85ሺህ ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ ነው፡፡

የህብረተሰቡን ፍላጎት በመመልከት ወደፊት እንደ አዲስ ግንባታቸው በሚጀመርባቸው የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታዎች ላይ የስቱዲዮ ቤት ግንባታ እንደማይኖርም ነው የገለጹት፡፡

በ2005 ዓ.ም ለቤቶች ግንባታ ከ4.7 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

መንግስት በሚቀጥሉት ሰባት አመታት ውስጥ ሁሉንም የከተማዋ የቤት ፕሮግራሞች ለማጠናቀቅ መታቀዱንም ኤጀንሲው ይፋ አድርጓል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s